ኤርምያስ 12:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞችህና የገዛ ቤተ ሰብህ፣ እነርሱ እንኳ አሢረውብሃል፣ በአንተም ላይ ይጮኻሉ፤ በመልካም ቢናገሩህም እንኳ አትመናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞችህና የቅርብ ዘመዶችህ ከድተውሃል፤ በአንተ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፤ ስለዚህ በፊትህ ስለ አንተ መልካም ነገር ቢናገሩም አትመናቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር ክደውሃልና፥ ጮኸውም በስተኋላህ ተሰበሰቡ፤ በመልካምም ቢናገሩህ አትመናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፥ በመልካምም ቢናገሩህም አትታመናቸው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል የሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበት፣ ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣ በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣ “ዛፉን ከፍሬው ጋራ እንቍረጥ፤ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ” ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።
“እንግዲህ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹና፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር፤ አለዚያ በእጃችን ትሞታለህ’ ለሚሉህ ለዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።
“ሐሰትን ለመናገር፣ ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤ በእውነት ሳይሆን፣ በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤ እኔንም አላወቁኝም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤ እውነትን የሚናገር የለም፤ ሐሰትን ይናገሩ ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።