ኤርምያስ 12:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስንዴን ይዘራሉ፤ እሾኽን ያጭዳሉ፤ ይደክማሉ፤ የሚያገኙት ግን የለም። ከእግዚአብሔርም ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ በመኸራችሁ ውጤት ታፍራላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፤ እራሳቸውን አደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፤ ስለ ጌታ ጽኑ ቁጣ በፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ስንዴ ዘርተው እሾኽ ሰበሰቡ፤ በሥራ እጅግ ደክመው ምንም ትርፍ አላገኙም፤ ከብርቱ ቊጣዬ የተነሣ በምርታቸው መጥፋት አዘኑ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስንዴን ትዘራላችሁ፤ እሾህንም ታጭዳላችሁ፤ ዕጣችሁም ምንም አይጠቅማችሁም፤ ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ በአዝመራችሁ ታፍራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፥ ደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፥ ስለ እግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከፍሬያችሁ ታፍራላችሁ። |
ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።
ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤ እውነትን የሚናገር የለም፤ ሐሰትን ይናገሩ ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።
እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ በሽታ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኵሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤ የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።
ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለ ሮጣችሁ ነው፤