ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር።
ኤርምያስ 10:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል። የእጅ ጥበብ ባለሙያና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞያተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ሐምራዊ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር፥ ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፥ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። |
ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር።
ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር።
“ ‘ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ፣ ተርሴስ ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር፤ ብርና ብረት፣ ቈርቈሮና እርሳስ አምጥታ ሸቀጥሽን ትለውጥ ነበር።
የመርከቦችሽ ሸራ ጥልፍ ሥራ ያለበት የግብጽ በፍታ ነበረ፤ ይህም እንደ ዐርማ አገለገለሽ። መጋረጃዎችሽ ከኤሊሳ ጠረፍ የመጡ፣ ባለሰማያዊና ሐምራዊ ቀለም ነበሩ።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፤ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጕዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።
ዕንጨቱን፣ ‘ንቃ!’ ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ፣ ‘ተነሣ!’ ለሚል ወዮለት! በውኑ ማስተማር ይችላልን? እነሆ፤ በወርቅና በብር ተለብጧል፤ እስትንፋስም የለውም።”