ኤርምያስ 10:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከጫካ ይቈርጣሉ፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ በመሣሪያው ቅርጽ ያበጅለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሞያተኛውም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሕዛብ ልማዳዊ እምነት ከንቱ ነው፤ ዛፍ ከደን ይቈረጣል፤ አናጢ በመሮ ቅርጽ ያወጣለታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ከዱር በመጥረቢያ እንደሚቈረጥ፥ በሠራተኛም እጅ እንደሚሠራ እንጨት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እንጅ በመጥረቢያ ይሠራል። |
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን? ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን? አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።
ብርታቴና ምሽጌ፣ በመከራ ቀን መጠጊያዬ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አሕዛብ ከምድር ዳርቻ፣ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “አባቶቻችን ለአንዳች ነገር ያልረቧቸውን ከንቱ ጣዖቶች፣ የሐሰት አማልክትን ወረሱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣ ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣ ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?
ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”
ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የእስያ አውራጃ የሚገኘውን በርካታ ሕዝብ እያሳመነ እንዳሳታቸው ይኸው የምታዩትና የምትሰሙት ነገር ነው፤ በሰው እጅ የተሠሩ አማልክት በፍጹም አማልክት እንዳልሆኑ ይናገራልና።
እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።