ኤርምያስ 10:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአሕዛብን መንገድ አትከተሉ፤ እነርሱ በሰማይ ምልክቶች ይታወካሉ፣ እናንተ ግን በእነዚህ አትረበሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፥ ከሰማይ ምልክቶችም የተነሣ አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን አካሄድ አትከተሉ፤ መቼም አሕዛብ ያልተለመደ አዲስ ነገር በሰማይ ባዩ ጊዜ በፍርሃት መንቀጥቀጥ ልማዳቸው ነው፤ እናንተ ግን በዚህ አትሸበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፤ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፥ አሕዛብ ይፈሩታልና። |
“ ‘እናንተም፣ “ለዕንጨትና ለድንጋይ እንደሚሰግዱ እንደ አሕዛብ፣ በዓለምም እንደሚኖረው ሕዝብ ሁሉ እንሁን” አላችሁ፤ ነገር ግን በልባችሁ ያሰባችሁት ከቶ አይሆንላችሁም።
እናንተንም፣ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ በምድራቸው ላይ የምትኖሩባቸው የአሞራውያንን አማልክት አታምልኩ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን አላዳመጣችሁኝም።”