ያዕቆብ 2:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁ ሥራ የሌለው እምነት በራሱ የሞተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚሁም ከሥራ የተለየ እምነት በራሱ የሞተ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመልካም ሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው። |
ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።