ኢሳይያስ 7:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፤ “አንተና ልጅህ ሸአር ያሹብ አካዝን ለመገናኘት ወደ ልብስ ዐጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፤ “‘አንተና ልጅህ ሸአር-ያሹብ አካዝን ለመገናኘት ወደ ልብስ አጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኩሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፤’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “አንተና ልጅህ ሼርያሹብ ንጉሥ አካዝን ለመገናኘት ውጡ፤ እርሱንም ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚመጣበት በልብስ አጣቢዎች ቦታ ታገኙታላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው፥ “አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው መታጠቢያ ቦታ ውጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው፦ አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፥ |
የአሦር ንጉሥ ከለኪሶ የጦሩን ጠቅላይ አዛዥ፣ ዋና አዛዡንና የጦር መሪውን ከታላቅ ሰራዊት ጋራ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣ ወደ ልብስ ዐጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የላይኛው ኵሬ ውሃ ቦይ በሚወርድበት ስፍራ ሲደርሱ ቆሙ።
በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወኑ ሌሎች ተግባራትና፣ ጀግንነቱ ሁሉ ኵሬውንና ውሃውን ወደ ከተማዪቱ ያመጣበትን የመሬት ለመሬት ቦይ እንዴት አድርጎ እንደ ሠራው በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?
ከርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዥ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር ትይዩ እስከ ሰው ሠራሹ ኵሬና የጀግኖች ቤት ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን መልሶ ሠራ።
ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እንድታገኘውም በአባይ ዳር ተጠባበቅ፤ ወደ እባብ ተለውጣ የነበረችውንም በትር በእጅህ ያዝ።
ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከታችሁም፤ ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።
የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን ከብዙ ሰራዊት ጋራ ከለኪሶ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወዳለበት፣ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። የጦር አዛዡም ወደ ልብስ ዐጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ፣ በላይኛው ኵሬ ቦይ አጠገብ ደርሶ ቆመ፤
ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”