ሆሴዕ 3:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ለብዙ ዘመን ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፣ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዐምደ ጣዖት፣ ያለ ኤፉድና ያለ ጣዖት ምስል ይኖራሉና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤ ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፥ |
ራሔል የጣዖታቱን ምስል ከግመሏ ኮርቻ ሥር ሸሽጋ፣ በላዩ ተቀምጣበት ነበር፤ ላባም ድንኳኑን አንድ በአንድ በርብሮ ምንም ሊያገኝ አልቻለም።
ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።
እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋራ ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋራ ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል።
የሚሠሯቸው መጐናጸፊያዎች የደረት ልብስ ኤፉድ ቀሚስ፣ ጥልፍ ሸሚዝ፣ ጥምጥምና መታጠቂያ ናቸው፤ ካህን ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ የተቀደሱ መጐናጸፊያዎችን ለአሮንና ለወንድ ልጆቹ ይሠራሉ።
በሮቿ ወደ ምድር ሰመጡ፤ የብረት መወርወሪያዎቻቸውን ሰባበረ፤ አጠፋቸውም፤ ንጉሧና መሳፍንቷ በአሕዛብ መካከል ተማርከው ተሰድደዋል፤ ሕጉ ከእንግዲህ አይኖርም፤ ነቢያቷም ከእንግዲህ፣ ከእግዚአብሔር ራእይ አያገኙም።
ከዋና ቅርንጫፎቿ ከአንዱ እሳት ወጣ፤ ፍሬዋንም በላ። በትረ መንግሥት የሚሆን፣ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ አልተረፈም።’ ይህ ሙሾ ነው፤ ለሐዘን እንጕርጕሮም ይሆናል።”
“ ‘እናንተም፣ “ለዕንጨትና ለድንጋይ እንደሚሰግዱ እንደ አሕዛብ፣ በዓለምም እንደሚኖረው ሕዝብ ሁሉ እንሁን” አላችሁ፤ ነገር ግን በልባችሁ ያሰባችሁት ከቶ አይሆንላችሁም።
የባቢሎን ንጉሥ በጥንቈላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ ጐዳናዎች መጋጠሚያ ላይ ይቆማል፤ ቀስቶቹን በመወዝወዝ ዕጣ ይጥላል፤ አማልክቱን ያማክራል፤ ጕበትንም ይመረምራል።
“የጦር ሰራዊቱም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ።
አለቃው ከብዙዎች ጋራ ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕትና ቍርባን ማቅረብን ያስቀራል። የታወጀው ፍርድ በርሱ ላይ እስኪፈስስ ድረስ፣ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያቆማል።”
አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰው፤ መቀነት አስታጠቀው፤ ቀሚስ አጠለቀለት፤ ኤፉድ ደረበለት፤ በልዩ ጥበብ በተጠለፈው መታጠቂያ ኤፉዱን አስታጠቀው፤ በላዩም አሰረው፤
ተራፊም አሳሳች ነገር ይናገራል፤ ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ፤ የውሸት ሕልም ይናገራሉ፤ ከንቱ መጽናናት ይሰጣሉ፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ተቅበዘበዙ፤ እረኛ በማጣትም ተጨነቁ።
“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
እነርሱ ግን፣ “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፣ “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አለ። የካህናት አለቆችም፣ “ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱለት።
የላይሽን ምድር ሰልለው የነበሩት ዐምስቱ ሰዎች ለወንድሞቻቸው፣ “ከእነዚሁ ቤቶች በአንዱ ኤፉድ፣ ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ዕወቁበት” አሏቸው።
ጌዴዎን በወርቁ ኤፉድ ሠራ፤ በተወለደበትም ከተማ በዖፍራ አኖረው። እስራኤልም በሙሉ ኤፉዱን በማምለክ ስላመነዘሩ፣ ኤፉዱ ለጌዴዎንና ለቤተ ሰቡ ወጥመድ ሆነ።
ኤፉድ ይለብስ የነበረውም አኪያ በመካከላቸው ነበር። እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ ነበር። ዮናታን አለመኖሩን ግን ያወቀ ሰው አልነበረም።
ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”
ካህኑም፣ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል ከፈለግህ ውሰደው፤ ከርሱ በቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።
ንጉሡም ዶይቅን፣ “እንግዲያውስ አንተው ዙርና ካህናቱን ግደላቸው” ብሎ አዘዘው። ኤዶማዊው ዶይቅም ዞረና ገደላቸው። በዚያች ዕለት ሰማንያ ዐምስት የበፍታ ኤፉድ የለበሱ ካህናትን ገደለ።