ሐጌ 2:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ ይኸውም ከዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት እስከ ተጣለበት ቀን ድረስ ያለውን ዘመን አስተውሉ፤ ልብ ብላችሁም አስቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ጊዜ ልብ በሉ፤ የጌታ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ዘጠነኛው ወር ከገባ ከዛሬ ከኻያ አራተኛው ቀን ጀምሮ አስተውሉ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ አስተውሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፣ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ። |
“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣሉ፤ የሚፈጽሙትም የርሱ እጆች ናቸው። ከዚያም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
“ዘሩ ጥሩ ሆኖ ይበቅላል፤ ወይኑ ፍሬውን ያፈራል፤ ምድሪቱ አዝመራዋን ታበረክታለች፤ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለቀሪው ሕዝብ ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ሲጣል፣ በዚያ የነበሩ ነቢያት የተናገሩትን ቃል አሁን የምትሰሙ ሁሉ፣ ለመገንባት እጃችሁን አበርቱ።