ሐጌ 2:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሐጌ እንዲህ አለ፤ “ ‘ይህ ሕዝብና ይህ ወገንም በፊቴ እንደዚሁ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የእጃቸው ሥራና የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል ጌታ፤ የእጆቻቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፤ በዚያ ያቀረቡትም ርኩስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐጌም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ በሙሉ እንደዚያው ነው፤ ስለዚህ ሥራቸውና የሚያቀርቡት ቊርባን የረከሰ ነው” ይላል እግዚአብሔር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፣ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፣ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፥ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው። |
ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።
የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈስሱም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሠኘውም፤ እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ። ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።
ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሯቸውና ኅሊናቸው የረከሰ ነው።
አንዳንዶችን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኗቸው፤ ለሌሎች ደግሞ በርኩስ ሥጋ የተበከለውን ልብሳቸውን እንኳ እየጠላችሁ በፍርሀት ምሕረት አሳዩአቸው።