ዘፍጥረት 7:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጹሕ ከሆኑትና ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት፣ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ጥንድ ጥንድ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንጹሕ እንስሳ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰውም ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ ከሆኑትና ካልሆኑት ከያንዳንዱ ዐይነት እንስሶች ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንጹሓን ወፎችና ንጹሓን ካልሆኑ ወፎች፥ ከንጹሕ እንስሳ፥ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንጽሕ እንስሳ ንጽሕም ካልሆነው እንስሳ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀስውም ሁሉ፤ |
ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ።
ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ ዐብረዋቸው ገቡ።