ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ ዐብረዋቸው ገቡ።
ዘፍጥረት 7:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸው ፍጥረታት በሙሉ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ወደ ኖኅ በመምጣት መርከቧ ውስጥ ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ዓይነት እስትንፋስ ካላቸው ፍጥረቶች ከእያንዳንዱ ዓይነት ሁለት ሁለት እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት እስትንፋስ ካላቸው ፍጥረቶች ከእያንዳንዱ ዐይነት ሁለት ሁለት እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ መርከብ ውስጥ ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚበሩ ወፎችም ሁሉ ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። |
ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ ዐብረዋቸው ገቡ።
ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋራ ይኖራል፤ ነብርም ከፍየል ግልገል ጋራ ይተኛል፤ ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።