ዘፍጥረት 5:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሙንም “እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጕልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስሙንም፥ “ጌታ በረገማት ምድር፥ ከሥራችን እና ከእጅ ድካማችን፥ ይህ ያሳርፈናል” ሲል፥ ኖኅ ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ላይ ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስሙንም ከሥራዬ፥ ከእጄ ድካምና እግዚአብሔር ከረገማት ምድር ይህ ያሳርፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስሙንም፤ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። |
ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፉ፤ ሰዎችና እንስሳት በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች ከምድር ላይ ጠፉ፤ ኖኅና ከርሱ ጋራ በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ።
“ይህ ለእኔ የኖኅ ውሃ ምድርን ዳግመኛ እንዳያጥለቀልቃት እንደማልሁበት፣ እንደ ኖኅ ዘመን ነው፤ አሁንም አንቺን ዳግም እንዳልቈጣ፣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።
በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ ቢኖሩባትም እንኳ፣ በጽድቃቸው ራሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችን ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም።
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈርቶ ቤተ ሰዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት ሠራ፤ በእምነቱ ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
እነዚህ በወህኒ የነበሩት ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እንቢተኞች ናቸው፤ በውሃ የዳኑት ጥቂት፣ ይኸውም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።