ዘፍጥረት 45:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በወንድሙ በብንያም ዐንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ብንያምም እያለቀሰ ዮሴፍን ዐቀፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድሙን የብንያምንም አንገት አቅፎ አለቀሰ፥ ብንያምም በአንገቱ ላይ አለቀሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የወንድሙን የብንያምን አንገት ዐቅፎ አለቀሰ፤ ብንያምም ወንድሙን ዐቅፎ አለቀሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድሙን የብንያምንም አንገት አቅፎ አለቀሰ፤ ብንያምም በአንገቱ ላይ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድሙን የብንያምንም አንገት አቅፎ አለቀሰ ብንያምም በአንገቱ ላይ አለቀሰ። |
ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደ ደረሰ፣ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረዥም ጊዜ አለቀሰ።