እናንተ፣ ‘እኛ ባሮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከዚያም ግብጻውያን ከብት አርቢዎችን እንደ ጸያፍ ስለሚቈጥሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
ዘፍጥረት 45:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆችህን፣ የልጅ ልጆችህን፣ በጎችህን፣ ፍየሎችህን፣ ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፥ ከእኔም በቅርበት፥ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆችህን፥ የልጅ ልጆችህን፥ በጎችህን፥ ፍየሎችህን፥ ከብቶችህን ሌላም ያለህን ነገር ሁሉ ይዘህ ና፥ በእኔው አቅራቢያ በሚገኘው በጌሴም ምድር ትኖራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐረብ በኩል በጌሤም ምድርም ትቀመጣለህ፤ ወደ እኔም ትቀርባለህ። አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ፥ የአንተ የሆነው ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እኔ ና አትዘግይ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ ወደ እኔም ትቀርባለህ አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፤ |
እናንተ፣ ‘እኛ ባሮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከዚያም ግብጻውያን ከብት አርቢዎችን እንደ ጸያፍ ስለሚቈጥሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው።
ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።
የግብጽ ምድር እንደ ሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኀላፊዎች አድርጋቸው።”
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።
“ ‘በዚያች ዕለት ግን ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሤምን ምድር የተለየች አደርጋታለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር በዚህች ምድር እንዳለሁ ታውቅ ዘንድ የዝንብ መንጋ በዚያ አይኖርም።