La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 42:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለ ሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማቸው አላወቁም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለ ሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማቸው አላወቁም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ እነርሱ የሚሉትን ሁሉ ያዳምጥ ነበር፤ እነርሱ ግን ከዮሴፍ ጋር የሚነጋገሩት በአስተርጓሚ ስለ ነበር የእነርሱን ንግግር ዮሴፍ እንደሚሰማቸው አላወቁም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም ዮሴፍ ነገ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ሰ​ማ​ባ​ቸው አላ​ወ​ቁም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ተ​ር​ጓሚ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም ዮሴፍ ነገራቸውን እንደሚስማባቸው አላወቁም በመካከላቸው አስተርጓሚ ነበረና።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 42:23
6 Referencias Cruzadas  

ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”


ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ፣ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።


ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደ እነርሱ ተመልሶ እንደ ገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዐይናቸው እያየ አሰረው።


“ፊታችሁ ሆኜ የማናግራችሁ እኔ ዮሴፍ ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ብንያም በዐይናችሁ የምታዩት ነው።


ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋራ ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።