ዘፍጥረት 39:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት ያለው ማንም የለም፤ እርሱ ያልሰጠኝ ነገር ቢኖር፣ አንቺን ብቻ ነው፤ ያውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት እሠራለሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት ያለው ማንም የለም፤ እርሱ ያልሰጠኝ ነገር ቢኖር፥ አንቺን ብቻ ነው፤ ያውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታዬ በዚህ ቤት ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት የለውም፤ ከአንቺ በቀር በእኔ ቊጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለ ሆንሽ ነው፤ ታዲያ ይህን አስከፊ ኃጢአት በመፈጸም እግዚአብሔርን እንዴት አሳዝናለሁ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ ሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፋ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ? |
እግዚአብሔርም በሕልሙ እንዲህ አለው፤ “አንተ ይህን ያደረግኸው በቅን ልቡና መሆኑን ዐውቄአለሁ፤ በእኔም ላይ ኀጢአት እንዳትሠራ የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት ለዚሁ ነው።
ከዚያም አቢሜሌክ አብርሃምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? ምን በደልሁህና ነው በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ታላቅ የጥፋት መዘዝ ያመጣህብን? በእውነቱ መደረግ የማይገባውን ነው ያደረግህብን።”
የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፣ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ እግዚአብሔርን አላስደሰተውም ነበር።
ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በጣም በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ኀጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤
ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ አገረ ገዦች ግን ከምግቡና ከወይኑ ሌላ፣ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመጫን አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ረዳቶቻቸውም እንዲሁ ይጭኑባቸው ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ከመፍራቴ የተነሣ እንዲህ ያለውን አላደረግሁም።
እኔ ግን፣ “እንደ እኔ ያለ ሰው ሸሽቶ ይደበቃል? ወይም ደግሞ ሕይወቱን ለማዳን ሲል ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ይገባዋልን? አልሄድም!” አልሁ።
ልቧ ወጥመድና አሽክላ፣ እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣ ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤ አምላክን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
ያገኛቸው ሁሉ ይውጣቸዋል፤ ጠላቶቻቸውም፣ ‘እኛ በደለኞች አይደለንም፤ እነርሱ የአባቶቻቸውን ተስፋ እግዚአብሔርን፣ እውነተኛ ማደሪያቸው የሆነውን እግዚአብሔርን በድለዋል’ አሉ።
“ማንኛውም ሰው በዐደራ የተሰጠውን ወይም በመያዣነት የተቀበለውን በማጕደልና ባልንጀራውን በማጭበርበር ባይታመን፣ እግዚአብሔርንም ቢበድል ወይም ባልንጀራውን ቢቀማው ወይም ቢያታልለው፣
ነገር ግን ይህን ሳያውቅ ቀርቶ መገረፍ የሚገባውን ያህል ያደረገ አገልጋይ በጥቂቱ ይገረፋል። ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራ ከተቀበለም ብዙ ይጠበቅበታል።
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን በመለማመድ አይቀጥልም፤ የርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም።
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”