የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው።
ዘፍጥረት 38:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙም ዔር ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙም ዔር ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀነሰችም፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀነሰችም ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። |
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው።
የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።