La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 37:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በስተርጅና የወለደው ስለ ሆነ ያዕቆብ ዮሴፍን ከሌሎች ልጆች ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፤ ስለዚህም ጌጠኛ የሆነ እጀ ጠባብ ሰፋለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበር በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 37:3
10 Referencias Cruzadas  

ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደ ደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት ያጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤


ከዚያም የዮሴፍን እጀ ጠባብ ወሰዱ፤ አንድ ፍየልም ዐርደው እጀ ጠባቡን በደሙ ነከሩት።


በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስኪ እየው” አሉት።


ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ ጌጠኛ የሆነና በዚያ ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን ዐይነት ልብስ ለብሳ ነበር።


ከልብስሽ አንዳንዱን ወስደሽ የምታመነዝሪበትን መስገጃ ስፍራ አስጌጥሽበት፤ እንዲህ ዐይነት ነገር ከዚህ ቀደም አልታየም፤ ወደ ፊትም አይኖርም።


አብ ወልድን ይወድዳል፤ ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።


‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣ እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን? ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶች ለሲሣራ ደርሰውት፣ በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለዐንገቴ ይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’