ዘፍጥረት 30:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሔልም፣ “እግዚአብሔር ፈርዶልኛል፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ አወጣችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሔልም፦ እግዚአብሔር ፈረደልኝ፥ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ አለች፥ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሔልም “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፤ ጸሎቴንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች፤ በዚህም ምክንያት ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፤ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፤ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ” አለች፤ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሔልም፦ እግዚአብሔር ፈረደልኝ፥ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ስጠኝ አለች፤ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። |
ከዳን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።