ዘፍጥረት 25:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድያምም ልጆች ዔፋ፥ ዔፈር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድያምም ልጆች ዔፋ፥ ዔፈር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የቀጡራ ዘሮች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድያምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፋር፥ ሄኖኅ፥ አቢሮንና ቲያሮስ ናቸው። እነዚህም ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድይምም ስጆች ጌፌር ዔፌት ሄኖኅ እቢዳዕ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። |
እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከፋራንም ሰዎች ይዘው ወደ ግብጽ በመምጣት፣ ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገቡ። ንጉሡም ለሃዳድ ቤትና መሬት ሰጠው፤ ቀለብም አዘዘለት።
የግመል መንጋ፣ የምድያምና የጌፌር ግልገል ግመሎች ምድርሽን ይሞላሉ፤ ወርቅና ዕጣን ይዘው፣ የእግዚአብሔርን ምስጋና እያወጁ፣ ሁሉም ከሳባ ይመጣሉ።