አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ።
ዘፍጥረት 21:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሣራም፣ “እግዚአብሔር ሣቅ አድሎኛል፤ ስለዚህ፣ ይህን የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋራ ይሥቃል” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም፦ “እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፥ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣራም፥ “እግዚአብሔር ደስ አሰኘኝ፤ ይህን የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ደስ ይሰኛልና” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሣራም እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች። |
አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ።
በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
በልብሽም እንዲህ ትያለሽ፣ ‘እነዚህን የወለደልኝ ማን ነው? እኔ ሐዘንተኛና መካን፣ የተሰደድሁና የተጠላሁ ነበርሁ፤ እነዚህን ማን አሳደጋቸው? ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ ታዲያ፣ እነዚህ ከየት መጡ?’ ”
“አንቺ መካን፣ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፣ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር።
አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረ በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ።
ሐናም ዔሊን እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፤ በነፍስህ እምላለሁ፤ እዚህ ቦታ ላይ በአጠገብህ ቆማ ወደ እግዚአብሔር ስትጸልይ የነበረች ያች ሴት እኔ ነኝ።