በዚያችም ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ትልቋ ልጁ ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር።
ዘፍጥረት 19:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ታላቂቱ ልጅ ታናሺቱን፣ “እኔ ትናንትና ማታ ከአባቴ ጋራ ተኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፤ አንቺም ደግሞ ከርሱ ዘንድ ገብተሽ ተኚ፤ በዚህም የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር ማትረፍ እንችላለን” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፦ “እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፥ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ታላቂቱ ልጅ እኅቷን “ትናንት ማታ እኔ ከእርሱ ጋር ተኝቼአለሁ፤ ዛሬም እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረውና አንቺም አብረሽው ተኚ፤ በዚህ ዐይነት ሁለታችንም ከአባታችን ልጆች ወልደን ዘራችን እንዳይጠፋ እናድርግ” አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፥ “እነሆ፥ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እናጠጣው፤ አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፤ እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ ከአባታችንም ዘር እናስቀር። |
በዚያችም ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ትልቋ ልጁ ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር።
በዚያችም ምሽት ደግሞ አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ትንሿ ልጁም ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።
ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም፤ ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።
ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በሚቀጡ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።