ዘፍጥረት 18:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ ዐምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን ይቅር አትልምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህን? ከተማይቱንስ በእርሷ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማዪቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? |
እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
አብርሃምም፣ “ጌታዬ አይቈጣ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እርሱም “ስለ ዐሥሩ ስል አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።
“በኢየሩሳሌም መንገዶች እስኪ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደ ታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህችን ከተማ እምራታለሁ።