ዘፍጥረት 18:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ ዐብረህ ታጠፋለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ቀረበ ዓለም፦ “በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ በደል የሌለባቸውን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ቀረበ አለም፦ በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? |
እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፣ “እነሆ ኀጢአት የሠራሁትም የተሳሳትሁም እኔ ነኝ፤ እነዚህ ግን በጎች ናቸው፤ ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን” አለ።
መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤ አለዚያማ ደፍሮ፣ ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?’ ይላል እግዚአብሔር።
ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።
ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።
ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።