ዘፍጥረት 17:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአብርሃም ቤት ያሉ ወንዶች ሁሉ፣ በቤቱ የተወለዱትም ሆኑ ከውጭ በገንዘብ የተገዙ ከርሱ ጋራ ተገረዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤት የተወለዱትና በብር ከእንግዶች የተገዙት፥ የቤቱ ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤቱ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ ወንዶች ሁሉ ከአብርሃም ጋር ተገረዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤት የተወለዱትና በብር ከእንግዶች የተገዙት፥ የቤቱ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤት የተወለዱትና በብር ከእንግዶች የተገዙት የቤቱ ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ። |
ትክክለኛና ጽድቅ የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።”