ዘፍጥረት 16:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ያናገራትን እግዚአብሔርን፣ “ኤልሮኢ” ብላ ጠራችው፤ ምክንያቱም “የሚያየኝን አሁን አየሁት” ብላ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች፥ የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አጋርም “በእርግጥ የሚያየኝን እግዚአብሔርን በዐይኔ አይቼ በሕይወት ኖርሁን?” በማለት ያነጋገራትን ጌታ “ኤልሮኢ” አለችው፤ ትርጒሙም “የሚያየኝ አምላክ” ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና። |
ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።
የአባቴ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋራ ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ሰድደኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መከራዬን አይቶ፣ ልፋቴን ተመልክቶ ትናንት ሌሊት ገሠጸህ።”
ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “እግዚአብሔር ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።