ዘፍጥረት 15:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተ ልጆች ስላልሰጠኸኝ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም፦ ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፥ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ዘር ስላልሰጠኸኝ ሀብቴን የሚወርሰው በቤቴ የተወለደ አገልጋይ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም፥ “ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ የዘመዴ ልጅ እርሱ ይወርሰኛል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርስኛል አለ። |
አብራምም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ልጅ የቀረሁ ስለ ሆንሁ፣ የቤቴ ወራሽ የደማስቆ ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” አለው።
ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤቴም የተወለዱ ሌሎች ባሪያዎች ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ይልቅ ብዙ የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች ነበሩኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?