ከዚህም ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ይህን ነገረ፤ አብራም በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው በአሞራዊው መምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ ነበር። መምሬ፣ ወንድሞቹ ኤስኮልና አውናን የአብራም የኪዳን አጋሮቹ ነበሩ።
ዘፍጥረት 14:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቼ ከበሉትና ከእኔ ጋራ ከሄዱት ሰዎች ድርሻ በቀር ለራሴ አንዳች ነገር አልቀበልም፤ አውናን፣ ኤስኮልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለራሴ ምንም ነገር አልወስድም፤ የእኔ ሰዎች የያዙትን እንዲወስዱ እስማማለሁ፤ እንዲሁም የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቼ ዐኔር፥ ኤሽኮልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴኖች ከበሉት እህልና ከእኔ ጋር ከመጡት ድርሻ በቀር፥ አውናን፥ ኤስኮልም፥ መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ ቢሆን ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፤ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። |
ከዚህም ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ይህን ነገረ፤ አብራም በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው በአሞራዊው መምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ ነበር። መምሬ፣ ወንድሞቹ ኤስኮልና አውናን የአብራም የኪዳን አጋሮቹ ነበሩ።
ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።