ዘፍጥረት 1:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርም ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ስፍፎ ነበር። |
በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤ በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”
ሰማያትን የፈጠረ፣ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣ የመሠረታት፣ የሰው መኖሪያ እንጂ፣ ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቷልና።