ዘፍጥረት 1:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው በቀንና በሌሊት ላይ ሥልጣን እንዲኖራቸውና ጨለማን ከብርሃን እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዓልትንና ሌሊትንም እንዲመግቡ፥ በመዓልትና በሌሊትም መካከል እንዲለዩ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። |
በቀን እንድታበራ፣ ፀሓይን የመደበ፣ በሌሊት እንዲያበሩ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ያዘዛቸው፣ የሞገዱ ድምፅ እንዲተምም፣ ባሕሩን የሚያናውጥ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ እንዲህ ይላል፤