ኤፌሶን 5:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ የክርስቶስ አካል ብልቶች ነንና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም እኛ የአካሉ ክፍሎች ነን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛም የክርስቶስ አካል ክፍሎች ነን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ የአካሉ ሕዋሳት ነንና። |
ሰውነታችሁ የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? ታዲያ፣ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ ከዝሙት ዐዳሪ ብልቶች ጋራ አንድ ላድርገውን? ከቶ አይሆንም!
ይህ ሰው፣ አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ እየተጋጠመ ምግብንም እየተቀበለ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ከሚያድግበት ራስ ከሆነው ጋራ ግንኙነት የለውም።