ዘዳግም 9:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ተነሣ፤ ከግብጽ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋልና ፈጥነህ ከዚህ ውረድ፤ እኔ ካዘዝኋቸው ፈጥነው ፈቀቅ ብለዋል፤ ቀልጦ የተሠራ ጣዖትም ለራሳቸው አበጅተዋል” ብሎ ነገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዚያም ጌታ፥ ‘ተነሥ፥ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፥ ከግብጽ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ክፉ ነገር በማድረግ ረክሰዋል፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው ሠርተዋል’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ ‘ፈጥነህ ከተራራው ራስ ላይ ውረድ፤ ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ፥ ክፉ ነገር በማድረግ ረክሶአል፤ እኔ ከሰጠኋቸው ትእዛዝ ሁሉ ወዲያውኑ ርቀው፥ የሚያመልኩትን ጣዖት ለራሳቸው ሠርተዋል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፤ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ በድለዋልና፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋልና፥ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አድርገዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፤ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋል፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል፥ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አድርገዋል አለኝ። |
ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ምድር ከግብጽ የወጣችሁባትን ይህችን ዕለት አስታውሱ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ አውጥቷችኋል። እርሾ ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።
ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይወርድ ብዙ እንደ ቈየ ባዩ ጊዜ፣ ወደ አሮን ተሰብስበው፣ “ናና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ያ ከግብጽ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅም” አሉት።
እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ፣ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ ዐውቃለሁና። በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፣ እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ለቍጣ ስለምታነሣሡት፣ በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።”
በግብጽ ሳለህ አንተም ባሪያ እንደ ነበርህ፣ ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ እንዳወጣህ አስታውስ፤ ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ታከብረው ዘንድ አዘዘህ።
በርግጥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታችሁ እንደ ነበር ተመለከትሁ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስልም ለራሳችሁ አበጃችሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን ካዘዛችሁ መንገድ በፍጥነት ወጥታችሁ ነበር።
እንዲህም በማለት ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ በታላቅ ኀይልህ የተቤዠኸውንና በኀያል ክንድህ ከግብጽ ያወጣኸውን፣ ያንተ ርስት የሆነውን ሕዝብህን አታጥፋ።
እስራኤላውያን ግን ሌሎችን አማልክት ተከትለው አመነዘሩ፤ ሰገዱላቸውም እንጂ መሳፍንታቸውን አልሰሙም። አባቶቻቸው እግዚአብሔርን በመታዘዝ በሄዱበት መንገድ ሳይሆን፣ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሕግ በመከተል ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ።