እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ መናገሩን ከፈጸመ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት፣ ሁለቱን የምስክር ጽላት ለርሱ ሰጠው።
ዘዳግም 9:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላት እግዚአብሔር ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁበት ዕለት እግዚአብሔር ከተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ትእዛዞች ሁሉ በእነርሱ ላይ ነበሩባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፥ ተሰብስባችሁ በነበረበትም ቀን ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ እናንተ በተራራው ግርጌ በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማችሁትን ቃል በእጁ የጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በተራራው ላይ የነገረኝ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። |
እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ መናገሩን ከፈጸመ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት፣ ሁለቱን የምስክር ጽላት ለርሱ ሰጠው።
እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ።
እግዚአብሔር በስብሰባው ቀን፣ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የተናገራቸውንና ቀድሞ ጽፏቸው የነበሩትን ዐሥሩን ትእዛዞች በእነዚህ ጽላት ላይ ጻፋቸው። እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።
በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፣ “እንዳልሞት የአምላክህ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ” ብለህ አምላክህን እግዚአብሔርን የጠየቅኸው ይህን ነውና።
ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ቤት ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በአእምሯቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።