አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።
ዘዳግም 8:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስንዴና ገብስ፣ ወይንና የበለስ ዛፎች፣ ሮማን፣ የወይራ ዘይትና ማር የሚገኝባት ምድር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስንዴና ገብስ፥ የወይንና በለስ ዛፍ እንዲሁም ሮማን፥ የወይራ ዛፍና ማር ወደ ሞሉባት ምድር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስንዴና ገብስ፥ ወይንና በለስ፥ ሮማንና የወይራ ፍሬ፥ ማርም የሞላባት ናት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስንዴ፥ ገብስም፥ ወይንም፥ በለስም፥ ሮማንም ወደ ሞሉባት፥ ወይራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፥ |
አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።
ሰሎሞን ደግሞ ለኪራም ቤተ ሰብ ቀለብ እንዲሆን ሃያ ሺሕ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፣ ሃያ ሺሕ ኮር ንጹሕ የወይራ ዘይት ሰጠው፤ ይህን ባለማቋረጥ በየዓመቱ ለኪራም ይሰጥ ነበር።
ይኸውም የእናንተኑ ወደምትመስለው ምድር እህልና የወይን ጠጅ፣ ዳቦና የወይን ተክል፣ የወይራ ዛፍና ማር ወዳለባት እስካገባችሁ ድረስ ነው፤ እናንተም ሞትን ሳይሆን ሕይወትን ምረጡ።’ “ሕዝቅያስ፣ ‘እግዚአብሔር ይታደገናል’ በማለት ስለሚያሳስታችሁ አትስሙት።
እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣ ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።
ሰብልህንና ምግብህን ጠራርገው ይበሉብሃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይውጣሉ፤ በጎችህንና ከብቶችህን ይፈጃሉ፤ የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ያወድማሉ፤ የታመንህባቸውንም የተመሸጉ ከተሞች በሰይፍ ያጠፏቸዋል።
“ ‘ይሁዳና እስራኤል እንኳ ከአንቺ ጋራ ተገበያይተዋል፤ የሚኒትን ስንዴ፣ ጣፋጭ ቂጣ፣ ማር፣ ዘይትና በለሳን በማምጣት በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣ እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣
ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ይህንም ከሮማንና ከበለስ ጋራ በመሎጊያ አድርገው ለሁለት ተሸከሙት።
የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ።
እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈስሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።