ዘዳግም 7:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በዛሬው ቀን የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ለመከተል ጥንቃቄ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ እንድታደርገው ዛሬ ያዘዝኩህን ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፍርድ በጥንቃቄ ጠብቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዛሬ እኔ ያዘዝኩህን ትእዛዝ፥ ሕግና ሥርዓት በጥንቃቄ ጠብቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ታደርጓት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዛትን ትእዛዝና ሥርዐት፥ ፍርድንም ጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ታደርጋት ዘንድ እኔ ዛሬ ለአንተ የማዝዛትን ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድንም ጠብቅ። |
አሁንም እስራኤል ሆይ፤ በሕይወት እንድትኖሩ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር እንድትገቡና እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ ጠብቋቸውም።
እነዚህን ሕግጋት ብታዳምጥና በጥንቃቄ ብትጠብቃቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ከአንተ ጋራ የገባውን የፍቅር ኪዳኑን ይጠብቃል።