ዘዳግም 32:52 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ምድሪቱን ከሩቅ ሆነህ ታያታለህ እንጂ፣ ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሩቅ ሆነህ ምድሪቱን ባሻገር ታያለህ፤ ነገር ግን እኔ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ወደዚያች ምድር አትገባም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሩቅ ሆነህ ምድሪቱን ባሻገር ታያለህ፤ ነገር ግን እኔ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ወደዚያች ምድር አትገባም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱን ፊት ለፊት ታያለህ እንጂ ወደዚያች ምድር አትገባም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱን ፊት ለፊት ታያለህ እንጂ ወደዚያች እኔ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አትገባም። |
ወደ ፈስጋ ተራራ ጫፍ ውጣ፤ ወደ ምዕራብና ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅም ተመልከት። አንተ ዮርዳኖስን ስለማትሻገር፣ ምድሪቱን በዐይንህ ብቻ እያት።
“ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፣ ከዓባሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።
እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው ሰላም አሉት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩ መጻተኞችና እንግዶች መሆናቸውን ተገንዝበው ነበርና።