ዘዳግም 27:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንጋዮቹ ላይ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርገህ ጻፍባቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ ግልጽ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚያም ድንጋዮች ላይ የእግዚአብሔርን ሕግጋት ሁሉ በግልጥ እንዲነበቡ አድርገህ ጻፍ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተገለጠ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ። |
ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “እስራኤል ሆይ፤ ጸጥ ብለህ ስማ! አንተ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል፤
መሠዊያውንም የሠራው የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ፣ እስራኤላውያንን ባዘዛቸው መሠረት ሲሆን፣ ይህንም የሠራው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና የብረት መሣሪያ ባልነካው ድንጋይ ነው፤ በዚህም ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ የኅብረት መሥዋዕትም ሠዉ።