ዘዳግም 19:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው የገደለ ሁሉ እንዲሸሽባቸው አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር መንገዶችን ሠርተህ፣ በሦስት ክፈላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው የገደለ ሁሉ እንዲሸሽባቸው አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር መንገዶችን ሠርተህ፥ በሦስት ትከፈፍላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአንተም መንገድህን ታዘጋጃለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚያወርስህን ምድር ከሦስት አድርገህ ትከፍላለህ፤ ለነፍሰ ገዳይም ሁሉ መማጸኛ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሰ ገዳይ ይሸሽባቸው ዘንድ ወደ እነርሱ የሚወስደውን መንገድ ታዘጋጃለህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የሚያወርስህን ምድር ከሦስት አድርገህ ትከፍላለህ። |
ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤ አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ! ድንጋዩን አስወግዱ፤ ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።
በእናንተም ምክንያት እግዚአብሔር እኔን ተቈጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገርና አምላካችሁ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።