“አሕዛብ ጎረቤቶቻችን በሰንበት ቀን ለመሸጥ ሸቀጣ ሸቀጥ ወይም እህል ቢያመጡ፣ በሰንበት ወይም በማናቸውም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመቱም ምድሪቱን እናሳርፋለን፤ ዕዳንም ሁሉ እንሠርዛለን።
ዘዳግም 15:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ እያንዳንዱ አበዳሪ ለእስራኤላዊ ባልንጀራው ያበደረውን ይተውለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ ምሕረት ዐውጇልና፣ አበዳሪው፣ እስራኤላዊ ባልንጀራውን ወይም ወንድሙን ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ ለእስራኤላዊ ወገኑ ገንዘብ ያበደረ ሁሉ ያበደረውን ብድር ይሰርዝለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ መሰረዣ ዓመት ነው ብሎ ያወጀበት ዓመት ስለ ሆነ ከእስራኤላዊ ወገኑ ያበደረውን ገንዘብ ለመቀበል አይፈልግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምሕረቱም የሚገባ ትእዛዝ ይህ ነው፤ ባልንጀራህ ወይም ወንድምህ የሚከፍልህን ገንዘብ ሁሉ አትከፈል፤ የአምላክህ የእግዚአብሔር ምሕረት ተብላለችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምሕረቱም የሚገባ ወግ ይህ ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፤ የእግዚአብሔር ይቅርታ ታውጆአልና ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ አይሻ። |
“አሕዛብ ጎረቤቶቻችን በሰንበት ቀን ለመሸጥ ሸቀጣ ሸቀጥ ወይም እህል ቢያመጡ፣ በሰንበት ወይም በማናቸውም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመቱም ምድሪቱን እናሳርፋለን፤ ዕዳንም ሁሉ እንሠርዛለን።
‘አንተ ካልተቀበልኸው፣ ስለ ምን ብለን ጾምን? አንተ ከጕዳይ ካልቈጠርኸው፣ ስለ ምን ራሳችንን አዋረድን?’ ይላሉ። “ሆኖም በጾማችሁ ቀን የልባችሁን ታደርጋላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ትበዘብዛላችሁ።