ዘዳግም 15:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወገንህ የሆነ ዕብራዊ ወንድን ወይም ሴትን ገዝተህ ስድስት ዓመት ካገለገለህ፣ በሰባተኛው ዓመት በነጻ ይሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወንድምህን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግሉህ፥ በሰባተኛው ዓመት ነጻ አውጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወንድም ሆነ ሴት ከእስራኤላውያን ወገን አንድ ሰው ራሱን ባሪያ አድርጎ ለአንተ ቢሸጥልህ፥ ከስድስት ዓመት አገልግሎት በኋላ በሰባተኛው ዓመት ነጻ ታወጣዋለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተም ወንድምህን ዕብራዊዉን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግሉህ፤ በሰባተኛውም ዓመት ከአንተ ዘንድ አርነት አውጥተህ ልቀቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ወንድምህን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግሉህ፤ በሰባተኛውም ዓመት ከአንተ ዘንድ አርነት አውጣው። |
“ራሱን በባርነት ለእናንተ የሸጠውን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ በየሰባት ዓመቱ ነጻ ትለቅቃላችሁ፤ ስድስት ዓመት ከተገዛላችሁ በኋላ ነጻ ታወጡታላችሁ።” አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም ጆሯቸውንም ወደ እኔ አላዘነበሉም።