ዘዳግም 11:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ መካከል፣ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ መካከል፥ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተአምራቱንና እርሱ በግብጽ ንጉሥና በመላው አገሩ ላይ ያደረገውን ድንቅ ሥራ ሁሉ አይታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅም መካከል በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንና በሀገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ድንቅ ሥራዉን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ሥራውን፥ |
በግብጻውያን ሰራዊት፣ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፣ እናንተን ባሳደዷችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብጽ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን?
ታላላቅ ፈተናዎችን፣ ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን አምላክህ እግዚአብሔር አንተን ያወጣበትን ብርቱ እጅና የተዘረጋች ክንድ በገዛ ዐይንህ አይተሃል። አምላክህ እግዚአብሔር አሁን በምትፈራቸው ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያንኑ ያደርጋል።