ዘዳግም 10:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከብኤሮት ብኔያዕቃን፣ (ከያዕቃን ልጆች የውሃ ጕድጓዶች) ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤ ልጁ አልዓዛር በርሱ ምትክ ካህን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላዊያንም ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም እዚያ ሞቶ፥ እዚያው ተቀበረ፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (እስራኤላውያንም ከቤን ያዕቃን የውሃ ጒድጓዶች ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያው ሞቶ ተቀበረ፤ በእርሱም ምትክ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤልም ልጆች የማስቢ ወገን ከሚሆን ከኢያቅም ልጆች ቦታ ከቤሮስ ተጓዙ። በዚያም አሮን ሞተ፤ ተቀበረም፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ በዚያም አሮን ሞተ በዚያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። |
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።