La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 1:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናንተ፣ “በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ባዘዘንም መሠረት ወጥተን እንዋጋለን” ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ወደ ተራራማው አገር መሄድ ቀላል መስሎ ስለ ታያችሁ፣ እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ ተነሣችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“እናንተም፦ ‘ጌታን በድለናል፥ ጌታ አምላካችን ልክ እንዳዘዘን፥ እንወጣለን እንዋጋለንም’ ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እናንተም ‘ሙሴ ሆይ፥ እኛ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አሁን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ባዘዘን መሠረት እንዋጋለን’ ብላችሁ መለሳችሁ፤ ኮረብታማይቱን አገር መውረር ቀላል መስሎአችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ለውጊያ ተዘጋጀ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“እና​ን​ተም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ናል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ሁሉ እን​ወ​ጣ​ለን፤ እን​ዋ​ጋ​ማ​ለን ብላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ሁ​ልኝ። ከእ​ና​ን​ተም ሰው ሁሉ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ያዘ፤ ወደ ተራ​ራም ወጣ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር መውጣትን አቀለላችሁት።

Ver Capítulo



ዘዳግም 1:41
4 Referencias Cruzadas  

አንድ ሰው በተንኰል ሆነ ብሎ ሌላውን ቢገድል፣ ከመሠዊያዬ ተወስዶ ይገደል።


ሰው በራሱ ቂልነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል።


በለዓምም የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ እኔን ለመቃወም መንገዱ ላይ መቆምህን አላወቅሁም፤ አሁንም ደስ የማትሰኝ ከሆነ እመለሳለሁ” አለው።