እንዲህም አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልባቸው በመንገድህ ከሚሄዱት ባሪያዎችህ ጋራ የፍቅር ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም፤
ዳንኤል 9:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፤ ተናዘዝሁም፤ “ከሚወድዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ሁሉ ጋራ የፍቅር ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፤ ጌታ ሆይ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር በመናዘዝ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦ “ለሚወዱህና ትእዛዞችህን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅና መፈራት የሚገባህ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አምላኬም ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፥ ተናዝዤም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሚወድዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ጋር ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና የምታስፈራ አምላክ ሆይ፥ |
እንዲህም አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልባቸው በመንገድህ ከሚሄዱት ባሪያዎችህ ጋራ የፍቅር ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም፤
በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።
ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ወድቆ በሚጸልይበት፣ በሚናዘዝበትና በሚያለቅስበት ጊዜ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች የሚገኙበት እጅግ ብዙ የእስራኤል ማኅበር በዙሪያው ተሰበሰበ፤ እነርሱም እንደዚሁ አምርረው አለቀሱ።
ከዚያም እንዲህ አልሁ፤ “ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያከብሩ የፍቅርህን ቃል ኪዳን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፣ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤
“አሁንም አምላካችን ሆይ፤ ቃል ኪዳንህንና ዘላለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅ፣ ኀያልና የተፈራህ አምላክ ሆይ፤ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችንና በመሪዎቻችን፣ በካህናታችንና በነቢያታችን፣ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ የደረሰው ይህ ሁሉ መከራ በፊትህ እንደ ቀላል ነገር አይታይ።
ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤ በደሌንም አልሸሸግሁም፤ ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤ አንተም የኀጢአቴን በደል፣ ይቅር አልህ። ሴላ
በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅሽ፣ ክብርሽንም ለእንግዶች አማልክት፣ በየለምለሙ ዛፍ ሥር አሳልፈሽ በመስጠት፣ ለእኔ ባለመታዘዝሽ፣ በደለኛ መሆንሽን ይህን አንድ ነገር ብቻ እመኚ’ ” ይላል እግዚአብሔር።
ወደዚያም ገብተው ወረሷት፤ ነገር ግን አልታዘዙህም፤ ሕግህንም አልጠበቁም፤ እንዲያደርጉት ያዘዝሃቸውን ከቶ አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ሁሉ ጥፋት በላያቸው አመጣህ።
ዳንኤልም ዐዋጁ እንደ ወጣ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፤ መስኮቶቹ በኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ባሉበት በሰገነቱ ቀድሞ ያደርግ እንደ ነበረው በቀን ሦስት ጊዜ ተንበርክኮ ጸለየ፤ አምላኩንም አመሰገነ።
እነዚህን ሕግጋት ብታዳምጥና በጥንቃቄ ብትጠብቃቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ከአንተ ጋራ የገባውን የፍቅር ኪዳኑን ይጠብቃል።
ስለዚህም አምላክህ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቅ፤ እርሱ ለሚወድዱትና ትእዛዞቹን ለሚጠብቁት የፍቅሩን ኪዳን እስከ ሺሕ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ ታማኝ አምላክ ነው።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?