La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዳንኤል 8:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህም ነገር እያሰብሁ ሳለሁ፣ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አውራ ፍየል፣ መሬት ሳይነካ ምድርን ሁሉ እያቋረጠ በድንገት ከምዕራብ መጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም ራእይ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አንድ አውራ ፍየል ምድርን አቋርጦ እግሮቹ መሬት ሳይነኩ ከምዕራብ በኩል እየበረረ መጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ስመለከት፥ እነሆ፥ ከምዕራብ ወገን አንድ አውራ ፍየል በምድር ሁሉ ፊት ላይ ወጣ፥ ምድርንም አልነካም፥ ለፍየሉም በዓይኖቹ መካከል አንድ ታላቅ ቀንድ ነበረው።

Ver Capítulo



ዳንኤል 8:5
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በታላቅ ኀይል የሚገዛና የወደደውንም ሁሉ የሚያደርግ ኀያል ንጉሥ ይነሣል።


የምስሉ ራስ ከንጹሕ ወርቅ፣ ደረቱና ክንዶቹ ከብር፣ ሆዱና ጭኖቹ ከናስ የተሠሩ ነበሩ፤


“ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሣል፤ ቀጥሎም በናስ የተመሰለው ሦስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ መላውን ምድርም ይገዛል።


“ከዚያ በኋላ ተመለከትሁ፤ በፊቴ ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበሩት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው።


ጠጕራሙ ፍየል የግሪክ ንጉሥ ሲሆን፣ በዐይኖቹም መካከል ያለው ትልቁ ቀንድ የመጀመሪያው ንጉሥ ነው።


በወንዙ አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት፣ ባለሁለት ቀንዶች አውራ በግ ተንደርድሮ መጣበት፤ በታላቅ ቍጣም መታው፤


ፍየሉም ታላቅ ሆነ፤ ነገር ግን በኀይሉ በበረታ ጊዜ፣ ትልቁ ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት የሚያመለክቱ አራት ታላላቅ ቀንዶች በቀሉ።