ዳንኤል 8:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኡባልም፣ “ገብርኤል ሆይ፤ ለዚህ ሰው የራእዩን ትርጕም ንገረው” ብሎ የሚጮኽ የሰው ድምፅ ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኡላይ ወንዝ ማዶ “ገብርኤል ሆይ! ይህ ሰው የራእዩን ትርጒም እንዲረዳው አድርግ!” የሚል የሰው ድምፅ ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኡባልም ወንዝ መካከል፦ ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ። |
አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋራ ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ የለም።”
በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ፣ የዚህ ሁሉ እውነተኛ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት። “እርሱም መለሰልኝ፤ የእነዚህንም ነገሮች ትርጕም እንዲህ ሲል ነገረኝ፤
እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ። ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አሳይሃለሁ” አለኝ።
እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጕልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤
መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን እነግርህና ይህን የምሥራች አመጣልህ ዘንድ ተልኬአለሁ፤
“እኔ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲመሰክር መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያናት ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፣ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”