Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከኡላይ ወንዝ ማዶ “ገብርኤል ሆይ! ይህ ሰው የራእዩን ትርጒም እንዲረዳው አድርግ!” የሚል የሰው ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከኡባልም፣ “ገብርኤል ሆይ፤ ለዚህ ሰው የራእዩን ትርጕም ንገረው” ብሎ የሚጮኽ የሰው ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በኡባልም ወንዝ መካከል፦ ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 8:16
16 Referencias Cruzadas  

ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል በገሊላ ምድር ወደምትገኝ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ ከእግዚአብሔር ተላከ።


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን የምሥራች እንድነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ መጥቻለሁ።


በዔላም አውራጃ በግንብ በታጠረው በሱሳ ከተማ ሆኜ ራሴን በራሴ በራእይ አየሁ፤ በኡላይ ወንዝ አጠገብም ቆሜ ነበር።


“እኔ ኢየሱስ ይህን ምስክርነት እንዲሰጣችሁ መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያን ልኬአለሁ፤ እኔ የዳዊት የትውልድ ሐረግና ዘር ነኝ፤ የሚያበራ የንጋት ኮከብ ነኝ።”


ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ የሚድኑትን ሰዎች ለማገልገል የሚላኩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት አይደሉምን?


በዚያን ጊዜ “ጴጥሮስ ሆይ! ተነሥና እያረድክ ብላ!” የሚል ድምፅ ሰማ።


ከሳውል ጋር ይሄዱ የነበሩ ሰዎች ድምፅ እየሰሙ ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩትን አጥተው፥ ዝም ብለው ቆሙ።


የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው።


እኔም “ጌታዬ ሆይ! እነዚህ ፈረሶች የምን ምሳሌ ናቸው?” ብዬ ጠየቅሁት። እርሱም “የእነዚህ ፈረሶች ምሳሌነት ምን እንደ ሆነ አሳይሃለሁ፤


እኔም የመጣሁት በወገኖችህ ላይ በመጨረሻው ዘመን የሚደርስባቸውን ነገር ላስረዳህ ነው፤ ስለዚህ ከዚህም በቀር ወደፊት የሚሆነውን ነገር የሚገልጥ ሌላ ራእይ አለ።”


ማን እንደ ተናገረኝ ለማወቅ ወደ ኋላዬ ዞር አልኩ፤ ዞር ባልኩ ጊዜም ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ፤


እዚያም ቆመው ከነበሩት ወደ አንዱ ቀረብ ብዬ የዚህን ሁሉ እውነት ትርጒም ጠየቅሁት፤ እርሱም የዚህን ሁሉ ትርጒም ነገረኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios