የእሳት ወንዝ፣ ከፊት ለፊቱ ፈልቆ ይፈስስ ነበር፤ ሺሕ ጊዜ ሺሖች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤ የፍርድ ጉባኤ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።
ዳንኤል 7:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ፣ የዚህ ሁሉ እውነተኛ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት። “እርሱም መለሰልኝ፤ የእነዚህንም ነገሮች ትርጕም እንዲህ ሲል ነገረኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ቆመው ከነበሩት ወደ አንዱ ቀረብ ብዬ የዚህን ሁሉ እውነት ትርጒም ጠየቅሁት፤ እርሱም የዚህን ሁሉ ትርጒም ነገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ ስለዚህ ሁሉ እውነቱን ጠየቅሁት፥ እርሱም ነገረኝ፥ የነገሩንም ፍቺ አስታወቀኝ። |
የእሳት ወንዝ፣ ከፊት ለፊቱ ፈልቆ ይፈስስ ነበር፤ ሺሕ ጊዜ ሺሖች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤ የፍርድ ጉባኤ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።
እኔ ወደ ቆምሁበት ስፍራ እየቀረበ ሲመጣ፣ ደንግጬ በግንባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ራእዩ ስለ ዘመኑ ፍጻሜ እንደ ሆነ አስተውል” አለኝ።
ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።
“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።
ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “አታልቅስ፤ እነሆ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣ የዳዊት ሥር ድል ነሥቷል፤ እርሱ መጽሐፉን ሊከፍትና ሰባቱንም ማኅተሞች ሊፈታ ይችላል” አለኝ።