ዳንኤል 5:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ቤልሻዛር ከፊት ይልቅ ፈራ፤ ፊቱም እጅግ ተለወጠ፤ መኳንንቱም ግራ ገብቷቸው ተደናገጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ብልጣሶር እጅግ ስለ ጨነቀው ፊቱ ይብሱን እየገረጣ ሄደ፤ መኳንንቱም ግራ ገብቶአቸው የሚያደርጉትን አጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ብልጣሶር እጅግ ደነገጠ፥ ፊቱም ተለወጠበት፥ መኳንንቶቹም ተደናገጡ። |
እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?
ከዚህ በኋላ የምድር ነገሥታትና ገዦች፣ የጦር መኰንኖች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ፤